“መስቀል ፍቅር እና አንድነት የተገኘበት፣ ጥል የተሸነፈበት፣ እርቅ የታወጀበት ነው” ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ

14
ባሕር ዳር: መስከረም 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሚከበሩት የአደባባይ በዓላት መካከል የመስቀል ደመራ በዓል አንዱ ነው። በዓሉ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አሕጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ መስቀል የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር የታረቁበት፣ ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት የተገኘበት፣ ጥል የተሸነፈበት፣ እርቅ የታወጀበት በዓል መኾኑን ገልጸዋል።
በዓሉ ሲከበር ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የሰጠውን የማዳን ጸጋ እና በረከት በማሰብ ሊኾን ይገባልም ብለዋል።በዓሉ መንፈሳዊ በዓል በመኾኑ ምዕመናን ከሥጋዊ ተግባራት በመራቅ መንፈሳዊ ሥራዎችን መፈጸም እንዳለባቸው አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።የመስቀል በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ሰማይ እና ምድርን አንድ አድርጎ ያስታረቀበት በመኾኑ የሃይማኖቱ ተከታዮች ከልዩነት ተግባር በመራቅ ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር፣ ሰላምንም ማረጋገጥ ይገባቸዋል ብለዋል። በዓሉ የሰላም እና የበረከት እንዲኾንም ተመኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል ዓደባባይ በድምቀት እየተከበረ ነው።
Next article”የመስቀል በዓል ከፈተና በኋላ ድል እና መነሳት መኖሩን ያስተምራል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው