
ጎንደር: መስከረም 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ስማቸው አበበ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከማኅበረሰቡ ጋር በጋራ እየሠሩ መኾኑን ገልጸዋል።
በዓሉን በማክበር ሂደት ርችት እና መሰል የተከለከሉ ተግባራትን መፈፀም እንደማይቻልም አስታውቀዋል።
ወጣቶች ለሰላም ዘብ በመቆም ማገዝ አለባቸው ያሉት ኮማንደር ስማቸው ነዋሪዎች እንግዳ ነገር በአካባቢያቸው ሲመለከቱ ለጸጥታ ኀይል ጥቆማ እንዲሰጡም አሳስበዋል።
ኅብረተሰቡም ለጸጥታ ስጋት የኾኑ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለጸጥታ አካላት ጥቆማ መሰጠት እንዳለበትም አሳስበዋል።
በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በጋራ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:- ተስፋዬ ጋሹ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!