የባሕር በርን ጉዳይ ከግብ ለማድረስ የውስጥ አንድነትን ማጠናከር ይገባል።

4
ሁመራ፡ መስከረም 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሕልውና ጉዳይ መኾኑን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአንድነት እንደተጠናቀቀው ሁሉ የባሕር በሩን ጉዳይ ከግብ ለማድረስም የውስጥ አንድነትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።ትናንት የብዙ ወደቦች ባለቤት የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ አንድ ወደብ አጥታ መኖሯ ትክክል አለመኾኑን የአካባቢው ነዋሪ አቶ ጀጃው አበራ ለአሚኮ ተናግረዋል።የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ፍጆታዎች እና ፍላጎቶች እንደሚያድጉ ያነሱት አቶ ጀጃው ከዓለም ጋር ለመገናኘት እና ለመወዳደርም የባሕር በር ጉዳይ አንገብጋቢ መኾኑን አንስተዋል።
የባሕር በር ለአንዲት ሀገር የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ነው ያሉት ደግሞ ሌላኛው ነዋሪ ቀሲስ ጸጋዬ አስማረ ናቸው። ጎረቤት ሀገራትም ከዓባይ በመማር በሰላማዊ መንገድ የኢትዮጵያን ጥያቄ መቀበል እንዳለባቸው ጠቁመዋል። ቀሲስ ጸጋዬ ዓባይን ስንገድብ ተካፍለን እንብላ ነው ያልነው ብለዋል። የባሕር በር ጥያቄያችንም በተመሳሳይ ተካፍሎ ለመኖር በመኾኑ ጉዳዩ በሰላም እንዲያልቅ የሚመለከታቸው ሀገራት በበጎ መመልከት እንዳለባቸው ነው የተናገሩት። የባሕር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ በርካታ ፋይዳዎች አሉት ያሉት ደግሞ በሰላምና ግጭት አፈታት የሁለተኛ ዲግሪ ምሩቁ እያቸው ተሻለ ናቸው። ከእነዚህ ፋይዳዎች መካከል ኢኮኖሚ አንዱ መኾኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ገንዘብ እንደምታወጣም ተናግረዋል።የባሕር በር ለኢትዮጵያ የሕልውና ጉዳይ ነው ብለዋል። ዓድዋን ያሸነፍነው በአንድነታችን ነው፤ ዓባይን የገደብነውም በውስጥ ትብብራችን ነው። ስለኾነም የባሕር በርን ጉዳይ ከጫፍ ለማድረስ በሀገር ሰላም እና በውስጥ አንድነት ዙሪያ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበምሥራቅ ጎጃም ዞን የተሰማሩ የልማት ፕሮጀክቶች የአካባቢ እና የማኅበረሰብ ደኅንነትን ጠብቀው እንዲሠሩ እየተደረገ ነው
Next articleየጋራ እንጅ የግል ባሕር የለም።