ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ አበረታች ሥራዎች እየተሠሩ ነው።

1
ደሴ: መስከረም 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከደሴ ከተማ አሥተዳደር ሴቶች ጋር በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
አሚኮ ያነጋገራቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች የሰላም እጦት በሴቶች ላይ አካላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት እንደሚያደርስ ተናግረዋል።
በከተማቸው ያለውን የልማት እና የሰላም እንቅስቃሴ ቀጣይነት እንዲኖረው የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ሴቶች ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ምሳየ ከድር በ2017 ዓ.ም የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሠራ ሥራ ከ71 ሺህ በላይ ሴቶችን ማደራጀት መቻሉን ጠቁመዋል።
በ2018 በጀት ዓመትም ሴቶች ሰላማቸውን በማስጠበቅ በልማት ዘርፍ አይነተኛ ሚናን እንዲጫወቱም በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት።
የአማራ ክልል ሴቶች ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኅላፊ ብርቱካን ሲሳይ መንግሥት ለሴቶች በሰጠው ትኩረት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲሻሻል የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል
በጤናው ዘርፍ እናቶች ነፍሰ ጡር ሲኾኑ ክትትል እንዲያደርጉ እና የጤና መድኅን ተጠቃሚ እንዲኾኑ ማድረግ መቻሉንም ኀላፊዋ አንስተዋል።
በትምህርቱ ዘርፍም ሴቷ ተወዳዳሪ እና ተፎካካሪ እንድትኾን ለማድረግ አበረታች ሥራዎች በመከናዎናቸው ለውጥ እያመጣ መኸኑን ገልጸዋል።
የተለያዩ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን ዳር ለማድረስ እና ውጤታማ ለመኾን ሰላም ወሳኝ በመኾኑ ሴቶች በሰላም ዙሪያ ጠንክረው ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል።
በሰላም እጦት ሴቶች ግንባር ቀደም ተጎጅ መኾናቸውን ያመላከቱት ኀላፊዋ “የሰላም አምባሳደር መኾን አለብን” ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ሰልሀዲን ሰይድ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት እየተሠራ ያለው ሥራ ውጤታማ መኾኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለጸ።
Next articleሰላም የየትኛውም ማኅበረሰብ የጋራ ፍላጎት እንደኾነ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ።