ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀደም ሲል የነበረውን የተሳሳተ ትርክት የቀየረ ነው፡፡

3
ደብረ ማርቆስ: መስከረም 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በትብብር ያሳኩት፣ የሁሉም አሻራ ያረፈበት እና ለሀገር ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶችን ይዞ የመጣ ግዙፍ ፕሮጀክት እንደኾነ ሃሳባቸውን ለአሚኮ ያጋሩ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች እና የሥራ ኀላፊዎች ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ገነት በቀለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የይቻላል እሳቤን በተግባር የገለጠ፤ ኢትዮጵያውያን ከተባበሩ ማድረግ እንደሚችሉ ያሳየ ዳግም ዓደዋ ነው ብለዋል፡፡
የዘመናት የትውልድ ቁጭት የወለደው በተፋሰሱ ሀገራት በተለይ ግብጽ ታራምድ የነበረውን የተሳሳተ ትርክት የቀየረ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ውጤት የተገኘበት የልማት መስፈንጠሪያ አቅም መኾኑን የገለጹት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የደጀን ወረዳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ታማኝ ውቤ ናቸው፡፡
የደብረ ወርቅ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ይበልጣል አበበ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እንደ ሀገር ተስፋን ይዞ የመጣ እና በቀጣይ ለማሳካት ለታቀዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ትልቅ መነሳሳት እና አቅም የሚፈጥር ስለመኾኑም ተናግረዋል፡፡
የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ የኔዋ ደመቀ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ከማድረጉ ባሻገር የጋራ ብሔራዊ መግባባትን የፈጠረ የትውልድ አሻራ መኾኑንም አመላክተዋል፡፡
በቀጣይም የገጠመውን የሰላም እጦት ችግር ለመፍታት እና እንደ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባም ነው የጠቆሙት፡፡
ኢትዮጵያውያን በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሳዩትን አንድነት በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችም ላይ ማስቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleትምህርትን በወቅቱ መከታተል እና ለፈተናዎች በቂ ዝግጅት ማድረግ ለጥሩ ውጤት ያበቃል።
Next articleያሆዴ የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው።