ለ17 ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

2
ወልድያ፡ መስከረም 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ከ17 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል። የዞኑ ትምህርት መምሪያ ምክትል ኀላፊ ወንድወሰን አክሊሉ በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ለዚህም መምሪያው ከረጅ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመተባበር በክረምት ወቅት የትምህርት ቁሳቁስ አሠባሥቧል።
ከ17 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ተማሪዎችም የትምህርት ቁሳቁስና የደንብ ልብስ ድጋፍ መደረጉን ነው ያስረዱት። እስካሁን ከወረዳዎች፣ ከዞን መምሪያዎች፣ ከባለሃብቶች እና መንግሥታዊ ካልኾኑ ድርጅቶች 17 ሺህ 250 ደርዘን ደብተር 441 ባኮ እስክርቢቶ፣ 5 ሺህ አጋዥ መጻሕፍት እና 1 ሺህ 119 ቦርሳዎች ተሠብሥቧል።
እንደ ዞን ድጋፍ ለሚሹ 25 ሺህ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ መያዙን ኀላፊው ተናግረዋል። በመኾኑም ለቀሪ ተማሪዎች የሚኾን ተጨማሪ ድጋፍ ያሻልና በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ ግለሰቦችና ረጅ ድርጅቶች ትብብራቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት ለመከላከል በጋራ መሥራት ውጤት ላይ ያደርሳል፡፡
Next articleትምህርትን በወቅቱ መከታተል እና ለፈተናዎች በቂ ዝግጅት ማድረግ ለጥሩ ውጤት ያበቃል።