የኢ ቲኬቲንግ አገልግሎት የተጓዦችን እንግልት ማስቀረት ችሏል፡፡

4
ደብረማርቆስ: መስከረም 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ሥር በሚገኙ 22 መናኸሪያዎች የኢ ቲኬቲንግ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ዞኑ ገልጿል።
በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ እንግልትን የሚቀንስ ዲጂታል የኢ ቲኬቲንግ አሠራርን በመዘርጋት አላስፈላጊ የታሪፍ ጭማሪን ለመከላከል እና ለተገልጋዮቹ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ እንደሚገኝ የምሥራቅ ጎጃም ዞን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ላመሥግን አልማው ለአሚኮ ተናግረዋል።
በዞኑ በሚገኙ የመናኸሪያ አገልግሎቶች የተጀመረው የኢ ቲኬቲንግ አገልግሎት የኅብረተሰቡን መጉላላት ከመቀነሱም በላይ ለተሽከርካሪ ሠራተኞችም የተሻለ አሠራርን እንዲከተሉ ያስቻለ ሥራ መኾኑንም ተናግረዋል።
የኢ ቲኬቲንግ አሠራር የሚስተዋሉ ብልሹ አሠራሮችንም ያስቀራል ብለዋል። በዞኑ ከ22 በላይ መናኸሪያዎች የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንዲኾኑ የተደረገ ሲኾን ተደራሽነቱን ለማስፋትም የማስተዋወቅ እና የግንዛቤ ሥራ መሠራቱንም ኀላፊው ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበአማራ ክልል ለበርበሬ ምርት ምን ያህል ትኩረት ተሰጥቷል?
Next articleበሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት ለመከላከል በጋራ መሥራት ውጤት ላይ ያደርሳል፡፡