የሱዳን መንግሥት ከታጣቂ ኃይሎች ጋር የሰላም ስምምነት ሊፈራረም ነው፡፡

224

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 04/2012 ዓ.ም (አብመድ) የሱዳን መንግሥት ከአማጺ ቡድኖች ጋር ሊስማማ መሆኑን የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ሰብሳቢው ሞሀመድ ሀምዳን ዳገሉ ናቸው ከታጣቂ ቡድኖች መሪዎች ጋር የተወያዩት፡፡ ውይይታቸውን ዋቢ አድርጎ ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበውም የሱዳን መንግሥትና አማጽያኑ ቅዳሜ ሰኔ 13/2012 ዓ.ም ስምምነት እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል፡፡

‘‘መንግሥት ሰላም እንዲሰፍን ቁርጠኛ ነው፤ ለሱዳን ሕዝብ ቃል የምንገባው ሁሉን አቀፍና ዘላቂ የሰላም ስምምነት ሰኔ 13 እንደምንፈርም ነው’’ ብለዋል የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢው፡፡

ከስምምነቱ በፊት የስልጣን ክፍፍል በሚደረግባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ዝግጅቶች እየተደረጉ ስለመሆኑም ዘገባው አንስቷል፡፡

ካለፈው ጥቅምት አንስቶ በደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ ድርድሮች ሲደረጉ ነበር፡፡ በጁባው ድርድር የሱዳን መንግሥት፣ የዳርፉር፣ ደቡብ ኮርዶፋንና የብሉ ናይል ግዛቶች አማጽያን ቡድኖች መሳተፋቸው ይታወሳል፡፡

በአብርሃም በዕውቀት

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleበአንድ ጀንበር ከመኖሪያ ቤትነት ወደ ሆስፒታልነት፡፡
Next articleየግብዓት አቅርቦት እጥረት የግብርና ሥራቸውን ወደተለመደው ልማዳዊ አሠራር እንዲያመሩት እያስገደደ መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግሩ፡፡