በግብርና መረጃ የበለጸጉ አርሶ አደሮችን ለመፍጠር ማሠልጠኛ ማዕከላት እየተጠናከሩ ነው፡፡

5

ደብረ ብርሃን: መስከረም 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ እያካሄደ ነው፡፡

 

በባለፈው በጀት ዓመት በዕቅድ ተይዘው የነበሩ ሥራዎች አፈጻጸም በአወንታ የሚወሰድ መኾኑን የመምሪያው ኀላፊ ታደሰ ማሙሻ ገልጸዋል፡፡

 

በየደረጃው ያሉ አካላት ግብርናን በቅርበት ለመደገፍ እና ዘርፉ ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ባሳዩት ቁርጠኝነት ምርታማነት ማደጉን ኀላፊው ጠቁመዋል፡፡

 

በዚህም በ2017 በጀት ዓመት በመኸር ዘመኑ በሰብል ልማት በዕቅድ ለመሠብሠብ የታሰበውን 17 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማሳካት መቻሉን አስታውሰዋል፡፡

 

በዚህ በጀት ዓመትም በግብርና መረጃ የበለጸጉ አርሶ አደሮችን ለመፍጠር የአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከላትን ማጠናከር ላይ በትኩረት ይሠራል ብዋል፡፡

 

ማዕከላቱን ለማጠናር እና አዳዲስ ግንባታዎችን ለማከናወን እስካሁን በ18 ወረዳዎች 31 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከአርሶ አደሮች መሠብሠቡን ጠቅሰዋል፡፡

 

በዚህ ሂደት ከ147 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል ብለዋል፡፡

 

በበጀት ዓመቱ በሁሉም የግብርና ዘርፎች የዞኑን የመልማት ጸጋዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ለተሻለ ምርታማነት በቅንጅት እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡

 

በዞኑ በመኸር ዘመኑ 556ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር የተሸፈነ ሲኾን ከ20 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡

 

ዘጋቢ፦ አበበች የኋላሸት

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኮሌራ በሽታን ለማጥፋት እየተሠራ ነው።
Next articleበምግብ ራስን የመቻል ፍጥነትን ለማሳለጥ በትኩረት ይሠራል።