ማኅበረሰቡ ጤናው ላይ እንዲያተኩር እየተሠራ ነው።

3

ወልድያ: መስከረም 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 ዕቅድ ትውውቅ አካሂዷል።

 

የቆቦ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሰለሞን ስንታየሁ አካባቢው ቆላማ በመኾኑ የወረርሽኝ ስጋት እንዳለበት ገልጸዋል። ካለፈው ዓመት አፈፃፀም በላቀ ወረርሽኝን ዜሮ በማድረግ የኅብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ታቅዷል ብለዋል።

 

የጋዞ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዮሴፍ በሪሁን የወረዳውን ማኅበረሰብ የጤና አጠባበቅ ግንዛቤ በማሳደግ መከላከል እና መታከም ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል ነው ያሉት።

 

የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ኀላፊ ሲስተር ፈለቁ መኮንን ማኅበረሰቡ ጤናው ተጠብቆ ልማት ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ መምሪያው አልሞ እየሠራ መኾኑንም አስረድተዋል።

 

ከወትሮው በተለዬ መልኩ የክልሉን የ25 ዓመት ዕቅድ መነሻ በማድረግ በሁሉም የጤና ዘርፍ ሰፊ ዕቅድ ታቅዷል ነው ያሉት።

 

በተመረጡ ጤና ኬላዎች የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ከመከላካከል ባለፈ ሕክምና እንዲሰጡ ይደረጋል ያሉት ኀላፊዋ የጤና ትምህርት ተደራሽነት እና ወረርሽኝን መከላከል ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ይሠራል ብለዋል።

 

የጤና መድኅን ተጠቃሚውን ቁጥር በመጨመር በአቅም እጥረት ምክንያት ተገቢውን ሕክምና ሳያገኝ የሚጎዳን ማኅበረሰብ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ እንደሚሠራም ኀላፊዋ ገልጸዋል።

 

ለዚህም ከመምሪያ እስከ ጤና ኬላ ያሉ ባለሙያዎች እና የሥራ ኀላፊዎች ተግባራቸውን ቆጥረው እንዲሠሩ ይደረጋል፤ ተገቢውም ክትትል እና ድጋፍም ይደረጋል ነው ያሉት።

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠንካራ የፍትሕ ሥርዓት መፍጠር በተያዘው በጀት ዓመት የሚጠበቅ ተግባር ነው። 
Next articleየኮሌራ በሽታን ለማጥፋት እየተሠራ ነው።