ሕዳሴ የአንድነት መገለጫ ነው።

2
ባሕር ዳር: መስከረም 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ በድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሕዝባዊ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል። ከድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በኅብረት ችለናል፤ ግድቡ የአንድነታችን መገለጫ ነው፤ ግድቡ የእኔ ነው የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል። በሰልፉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድል ለኛ ብቻ ሳይሆን ለተቀሩት አፍሪካ ወንድሞቻችን የኢኮኖሚ ነጻነት ማረጋገጥ እንደሚቻል ብርሃን ያሳየ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየቱሪዝም አውደ ጥናት እና አውደ ርዕይ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
Next article“የደብረ ታቦር አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ”