
አዲስ አበባ፡ መስከረም 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሆሳዕና ከተማ “ቱሪዝም ለዘላቂ ለውጥ” በሚል መሪ መልዕክት የቱሪዝም አውደ ጥናት እና አውደ ርዕይ መካሄድ ጀምሯል።
ቱሪዝም ሚኒስቴር የዓለም የቱሪዝም ቀንን አስመልክቶ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በመተባበር በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመጎብኘት የቱሪዝም ሳምንትን እያከበረ ይገኛል። የቱሪዝም ሳምንት ክብረ በዓሉ አንዱ አካል የኾነውና በክልሉ ርዕሰ ከተማ ሆሳዕና የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን የሚያስቃኝ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እና አውደ ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት መሪዎች እና ሌሎችም የቱሪዝም ዘርፍ ተዋንያን ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግሥቴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!