ሕዳሴ የመቻል ማሳያ ነው።

7
ባሕር ዳር: መስከረም 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በሀረሪ ክልል ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በኢትዮጵያውያን እየተባበረ ክንድ እና ጽናት የተገነባው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን መግለጻቸውን ቀጥለዋል። ዛሬ የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች በሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ምክንያት ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።
በድጋፍ እና በደስታ መግለጫ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በሕዝባዊ ሰልፉ የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ማንሠራራት ምልክት፤ የሕዳሴው ግድብ የብልጽግናችን አሻራ፤ ግድባችን የመቻል ማሳያ ነው፤ ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችን እና የአብሮነታችን ምሰሶ፤ ግድባችን የኅብረ ብሔራዊነታችን እና የአንድነታችን መሠረት ነው የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች መተላለፋቸውን ከሀረሪ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየመጣው አንጻራዊ ሰላም በግብር አሠባሠቡ ላይ አወንታዊ ለውጥ እያመጣ ነው።
Next articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦