የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከ840 ሺህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

6
ጎንደር: መስከረም 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከ840 ሺህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የትምህርት ቁሳቁስ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ናቸው። ድጋፉ 840 ሺህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት መኾኑን በዕለቱ ገልጸዋል።
በዞኑ ለሚገኙ አራት ወረዳዎች ማለትም ለደምቢያ፣ ለወገራ፣ ለጎንደር ዙሪያ እና ለላይ አርማጭሆ ወረዳዎች ነው ድጋፍ የተደረገው ብለዋል።
ድጋፉ የከተማዋ ነዋሪዎችን በማስተባበር የተገኘ መኾኑንም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አመላክተዋል። ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይኾኑ የሚያስችል መኾኑን ነው የገለጹት። መተጋገዝ እና አብሮነትም በመስኩ ያስፈልጋል ነው ያሉት ።
ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍ ነው ያሉት እና ድጋፉን የተረከቡት ደግሞ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሬ ናቸው።
ዘጋቢ:- ‎ቃልኪዳን ኃይሌ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሠብሠብ አቅዶ እየሠራ ነው።
Next articleየመጣው አንጻራዊ ሰላም በግብር አሠባሠቡ ላይ አወንታዊ ለውጥ እያመጣ ነው።