“የሕዳሴን ድል መርህ እና አርዓያ ያደረገ ልማት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ ይጠበቃል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

9

ባሕር ዳር: መስከረም 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።

የድጋፍ ሰልፉን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የታታሪ ሕዝቦች አምባ፣ የእንቁ ባሕላዊ እሴቶች መገኛ፣ የበርበሬ አምራቾቹ እና የእንሰት ወዳጆቹ ምድር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሕዳሴ መጠናቀቅ የልማት ሰንደቁን በድል አውለብልቧል ብለዋል።

የሕዳሴ ግድብ የተጠናቀቀው ተባብረው በሰሩ ክንዶች፤ በብስለት በተመሩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች፤ በተደመረ የሀገር ሃብት እና ትውልዳዊ ኃላፊነት መኾኑንም ገልጸዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ክልሉ የእስከዛሬ ስኬቶችን እሴት በማድረግ ለታላላቅ ሀገራዊ የልማት ግቦቻችን ያለውን መሻት ያሳየ ነው ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ልዕልና ከላብ እስከ ደም ጠብታ የመታገል፤ ሀገር በምትፈልገን በሁሉም የልማት ሰልፎች ፊት ቀድሞ የመገኘት የጋራ አቋምን ዛሬ በድጋፍ ሰልፉ አይተናል ነው ያሉት።

የሕዳሴን ድል መርህ እና አርዓያ ያደረገ ልማት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ ይጠበቃል ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየገበያ ማዕከል መገንባት የንግድ ሥርዓቱን ያዘምነዋል።
Next article“በዕቅድ የመመራት ልምድ ውጤታማ አድርጎኛል” ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተማሪ