
ባሕር ዳር: መስከረም 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ እና የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ከከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኀላፊዎቹ በተጨማሪ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችም ተገኝተዋል።
መሪዎቹ በጉብኝታቸው የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከክልሉ፣ ከፌደራል መንግሥት እና ከሕዝቡ ጋር በጋራ በመኾን ያስገነባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአይራ 2ኛ ደረጃ የግብይት ማዕከል፣ የአዘዞ የምገባ ማዕከል፣ የስማርት ሲቲ ማስተባበሪያ ማዕከል፣ የጅንዓድ ፒያሳ መዝናኛ ማዕከል፣ የወለቃ የደሮ እና የዓሳ እርባታ ማዕከል በከተማ አሥተዳደሩ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የሚኾኑ ፕሮጀክቶች መኾናቸው ተጠቁሟል።
ዘጋቢ፦ መሠረት ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!