
ፍኖተ ሰላም: መስከረም 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን የ2017 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ በፍኖተ ሰላም ከተማ እያካሄደ ነው።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓባይ ዓለሙ በመሪዎች ቁርጠኝነት እና በጸጥታ አካሉ መሰዋዕትነት በዞኑ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር በአንጻራዊነት እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።
ወቅቱ የሕዳሴ ግድብን በማስመረቅ እና ለሕዝቡ ይፋ በማድረግ የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን መኾኑን ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል።
በቀጣይ ዞኑን ከገባበት የፖለቲካ እና የጸጥታ ችግር ለማውጣት በቁጭት እና በትጋት የምንሠራበት ዓመት ይኾናል ነው ያሉት።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዕድሜዓለም አንተነህ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አቅምን በመፈተሽ ማልማት፣ መገንባት እና ማጽናት ያስፈልጋል ብለዋል።
በቀጣይ በጀት ዓመት የልማት ሥራዎችን ለማሳካት “ትጋት፣ ቁርጠኝነት እና ቁጭት ያነገበ መሪ ማፍራት ያስፈልጋል” ነው ያሉት።
ከትናንት ውድቀት እየተጸጸተ ለነገ ስኬት የሚነሳ መሪ እና ባለሙያ በመፍጠር በትኩረት ለመሥራት መነሳት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
በተለይ አሁን ያለውን የጸጥታ ኹኔታ ሙሉ በሙሉ ለማረጋጋት እና በራስ አቅም ለመፍታት የምናጠናክርበት ዓመት እንዲኾን የምንሠራበት ይኾናል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!