
ጎንደር: መስከረም 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የአይራ የግብይት ማዕከልን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
የግብይት ማዕከሉ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በአንድ ማዕከል የሚያገኙበት የግብይት ማዕከል ነው። የግብይት ማዕከሉን ርእሰ መሥተዳድሩ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
162 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት የግብይት ማዕከሉ ከክልሉ እና ከተማ አሥተዳደሩ በተገኘ በጀት ተገንብቶ መጠናቀቁ ተገልጿል።
ከምረቃው ጎን ለጎን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች የተለያዩ የልማት ሥራዎች ያሉበትን ሁኔታ እየተመለከቱም ነው።
ዘጋቢ፦ ዳንኤል ወርቄ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!