የዓለም ቱሪዝም ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መከበር ጀመረ።

6

አዲስ አበባ፡ መስከረም 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው በቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ የተመራውን ልዑክ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለዋል። የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWT) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ1963 ዓ.ም ተቋቁሟል፡፡ በየዓመቱ መስከረም 17 በዓለም አቀፍ ደረጃ የዓለም የቱሪዝም ድርጅት (UNWT) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተቋቋመበት ቀን “የቱሪዝም ቀን” ተብሎ ስያሜውን በመያዝ እንዲከበር መወሰኑ ይታወቃል።

የዓለም ቱሪዝም ቀን እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉ ሀገራት ለቱሪዝም ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ቱሪዝም በሚያስገኘው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አስተዋፅኦ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማነሳሳት እና ግንዛቤ የመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተነስቷል። ይህም ስለታመነበት በሀገራችን ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ከተለያዩ ክልሎች ጋር በመተባበር በዓሉን በማክበር በየአካባቢው ስለቱሪዝም ጠቀሜታ ግንዛቤ ለመፍጠር እየተሠራ ነው።

ዘንድሮ “ቱሪዝምና ዘላቂ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ46ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ38ኛ ጊዜ ነው መስከረም 17 የሚከበረው። ከሀገራዊ አውድ ጋር የተጣጣሙ ልዩ ልዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዕለቱን ማክበር ተጀምሯል።

በቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ የተመራው ልዑክ የተለያዩ የመስህበ ስፍራዎችን እየጎበኘ ሆሳዕና ከተማ የገባ ሲሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለዋቸዋል።

በዓሉ በቀጣይ ቀናት የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን በመጎብኘትና አልምቶ መጠቀም ላይ በመወያየት ይከበራል። የከምባታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ‘መሳላ’ እና ሌሎች በዓላትን በመታደምም ይከበራል ተብሎ ይጠበቃል።

የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም ተገኝተው መስህቦችንና ሁነቶቹን ለዓለም እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግሥቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ፈተናዎች ቢበዙም እንኳ ካስቀመጥነው ግብ ለመድረስ ብርቱ መኾንን ያሻል” ውጤታማው ተማሪ
Next articleርእሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ የአይራ ግብይት ማዕከልን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።