
ጎንደር፡ መስከረም 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ቱጌዘር ዊ ለርን ኢትዮዽያ የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት በጎንደር ከተማ ወላጆቻቸው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 305 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ደብተር፣ እስክርቢቶ፣ እርሳስ፣ ቦርሳ እና የደንብ ልብስ ነው ድርጅቱ ድጋፍ ያደረገው።
ድጋፍ የተደረገላቸው የተማሪ ወላጆች ድርጅቱ ለልጆቻቸው ለትምህርት የሚያስፈልጉ የትምህርት ግብዓቶችን ድጋፍ ስላደረገላቸው አመሥግነዋል።
የቱጌዘር ዊ ለርን ኢትዮዽያ ሥራ አሥኪያጅ ታጠቅ እዘዘው ድርጅቱ በጎንደር ከተማ በ2018 የትምህርት ዘመን ያደረገው ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ850ሺህ ብር በላይ እንደኾነም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ተስፋዬ ጋሹ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!