“በሕዳሴ የታየው ትዕምርታዊ ተግባር ሕዝቦችን ዋና ተሳታፊና ተጠቃሚ ያደረገ የላቀ የልማት አፈጻጸም ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

10
ባሕር ዳር: መስከረም 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።
ሕዝባዊ ሰልፉን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተፈጥሮ በረከት የበዛለት፣ የበርካታ ቅመማ ቅመሞች መገኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከሕዳሴ መጠናቀቅ የልማት ጉልበትን ያገኛል ብለዋል።
በታላቁ የሕዳሴ ግድብ የታየው ትዕምርታዊ ተግባር ሕዝቦችን ዋና ተሳታፊና ተጠቃሚ ያደረገ የላቀ የልማት አፈጻጸም ነው።
በክልሉ የሕዳሴ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ትናንትን መነሻ በማድረግ እንደሀገር ወደ አለምናቸው የኢትዮጵያ ብልጽግና መዳረሻዎች ለመድረስ የጥንካሬ መንፈስን ይበልጥ የሚያድሱ ናቸው ነው ያሉት።የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች በሕዝባችን እና መንግሥታችን የጋራ ጥረት እንደተሳካው የሕዳሴ ግድባችን፣ በቀጣይም ተፈጥሮ ለክልሉ የለገሰቻቸውን እምቅ ፀጋዎች በማልማት ተደማሪ ድሎችን እንደሚቀዳጁ እምነት አለኝ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በመፍታት ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሠራል።
Next articleቱጌዘር ዊ ለርን ኢትዮዽያ የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።