የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በመፍታት ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሠራል።

7
ደብረ ማርቆስ: መስከረም 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ ትውውቅ ተካሂዷል።
በ2017 በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ የኾኑ ተግባራትን መሥራት የተቻለበት እንደነበር የተናገሩት የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ ናቸው። በ2018 በጀት ዓመት ሰላምን በማስፈን ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በሌሎችም ዘርፎች ስኬታማ ተግባራትን ለመሥራት በትኩረት የምንሠራበት ነው ብለዋል።
“አንድነታችን በማጠናከር የተቀመጡ ዕቅዶችን ለማሳካት በትኩረት መሥራት እንደሚገባም” መልዕክት አስተላልፈዋል። በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው እንደ ፓርቲ በ2017 በጀት ዓመት በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፍ ካለፉት ዓመታት በተሻለ የፈጸምንበት ነበር ብለዋል። በቀጣይም ፓርቲው የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በመፍታት ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አስገንዝበዋል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኀላፊ አየሁዓለም ያሳብ የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የመንግሥት ሠራተኛውን አቅም ማጎልበት ላይ መሠራቱንም ተናግረዋል፡፡የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ተመስገን ተድላ ባለፈው በጀት ዓመት ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት ተሠርቷል ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleጸጋን አሟጦ በመጠቀም ማኅበረሰቡን የልማት ተቋዳሽ ማድረግ ያስፈልጋል።
Next article“በሕዳሴ የታየው ትዕምርታዊ ተግባር ሕዝቦችን ዋና ተሳታፊና ተጠቃሚ ያደረገ የላቀ የልማት አፈጻጸም ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ