ግቦችን ለመፈጸም በዓላማ መጓዝ ይገባል።

4
ደብረ ታቦር፡ መስከረም 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር የ2017 ዓ.ም የመንግሥት የልማት ሥራዎችን ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመትን ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሄዷል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን በ2017 ዓ.ም በፀጥታው ላይ ከሁሉም አካላት ጋር ተናቦ በመሥራት ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል። በዚህም ለሌሎች የልማት ሥራዎች እንቅፋት የኾኑ ጉዳዮች መፍትሔ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ለ2018 ዓ.ም ዕቅድም ያለፉትን ድክመቶች በመፍታት ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል። “ይህ ዓመት የ25 ዓመቱ አሻጋሪ የልማት ዕቅድ ፍኖተ ካርታ የተዘጋጀበት ነው” ያሉት ከንቲባው ግቦችን ለመፈጸም በዓላማ መጓዝ ይገባል ብለዋል።
የተጓተቱ የልማት ሥራዎችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆኑም ነው የተናገሩት። የአማራ ክልል ምክር ቤት የግብርና፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ውኃ ሃብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከፍያለው ሙላቴ የዓድዋን ድል ከመዘከር ባለፈ ሌላኛውን የዓድዋ ድል የሚደግም ትውልድ እና መሪ መፈጠሩን ተናግረዋል። ለዚህም በሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ ዕውን ሆኖ የተመረቀው እና ዳግማዊ ዓድዋ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማሳያ መኾኑን አንስተዋል።
ወቅቱ እንደ ሀገር በቁጭት የሚጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ አዲስ የታሪክ እጥፋት የታየበት ጊዜ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
የተቀመጠውን አሻጋሪ የልማት ዕቅድ ወደ ተግባር በመቀየር ሀገርን ከድህነት ማውጣት እና የሀገሪቱን ከፍታ የሚያረጋግጡ ግቦችን ማሳካት የሁሉም ኀላፊነት እንደሆነም ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበህዳር ወር በሚካሄደው 10ኛው የከተሞች ፎረም ከ150 በላይ ከተሞች ይሳተፋሉ።
Next articleተስፋ የተጣለበት የፍኖተ ሰላም ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ምን ደረጃ ላይ ነው?