በህዳር ወር በሚካሄደው 10ኛው የከተሞች ፎረም ከ150 በላይ ከተሞች ይሳተፋሉ።

4
አዲስ አበባ፡ መስከረም 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአፍር ክልል የሚዘጋጀውን 10ኛውን የከተሞች ፎረም አስመልክቶ የመሰረተ ልማት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ፎረሙ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ከህዳር 06 እስከ 10/2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።
ፎረሙ “የከተሞች እድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ሲኾን ከ150 በላይ ከተሞችና ከ10 በላይ የግል እና የመንግሥት ድርጅቶች ይሳተፋሉ ብለዋል ሚኒስትሯ።
የሚሳተፉ ከተሞች የሠሯቸውን ሥራዎች ለአውደ ርዕይ በማቅረብ እርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ እንደሚካሄድም በመግለጫው ተነስቷል። የተለያዩ ጥናቶችም ቀርበው ውይይት ይካሄዳል ብለዋል ሚኒስትሯ በመግለጫቸው።
በፎረሙ የሚሳተፉ ከተሞች እስከ መስከረም 30 ምዝገባ በማካሄድ ለፎረሙ ዝግጅት ሊያደርጉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የከተሞች ፎገም መዘጋጀቱ የከተሞችን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ያሉት ሚኒስትሯ ከተሞችን የማወዳደሪያ መድረኮች በማዘጋጀት እና ለልማት በማፎካከር እድገትን ለማፋጠን እንሠራለን ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ራሔል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየኅብረት ሥራ ማኅበራት ገበያን ማረጋጋት እንዲችሉ መደገፍ እና አቅማቸውን ማሳደግ ይገባል።
Next articleግቦችን ለመፈጸም በዓላማ መጓዝ ይገባል።