“የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ የሕዳሴን ድል በሌሎች ልማቶች ለመድገም ተነስቷል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

9

ባሕር ዳር: መስከረም 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በብዝኃነት የደመቀውና የልማት አርበኛ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ የሕዳሴን ድል በሌሎች ልማቶች ለመድገም ተነስቷል ነው ያሉት።

ተባብሮ፣ በጋራ ተመካክሮ መልማትን እንደ እጁ መዳፍ ጠንቅቆ የሚያውቀው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ፤ በሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የድጋፍ ሰልፍ ያስተጋባቸው መልዕክቶች የእስከዛሬ ስኬቶቻችን ሳያዘናጉን ለተሻለው እንድንበረታ ጉልበት የሚሰጠን የሰላም እና የልማት ሰልፍ ነው ብለዋል።

ዛሬ በክልሉ የታየው ልማትን አጀንዳ ያደረገ ሰልፍ የማንሠራራት ዘመናችን መሰረት እንደያዘ ማሳያ ነው፡፡ የተስተጋቡት መፈክሮችም ሕዝቡ ለመንግሥት የሰጣቸው የልማት አደራዎች ጭምር እንደሆኑ ተገንዝበናል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎትን ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
Next articleየኅብረት ሥራ ማኅበራት ገበያን ማረጋጋት እንዲችሉ መደገፍ እና አቅማቸውን ማሳደግ ይገባል።