
ባሕር ዳር: መስከረም 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት የምስክር ማሕተም በሆነው አፋር ዛሬም የኢትዮጵያ ሰንደቅ በድል ሰልፍ ከፍ ብሎ ውሏል ብለዋል።
የአፋር መሬቱም ሰውም ለሀገር ሉዓላዊነት ዋጋ የከፈለ ጀግና ሆኖ ብቻ አይጠቀስም፤ የልማት ጮራ እየፈነጠቀበት ያለ የልማት አርበኞች ምድር ነው። የሕዳሴ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ልማት ለሚተጋው ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ ይሆነዋል ነው ያሉት።
በድጋፍ ሰልፉም የተስተጋባው የአፋር ሕዝብ ድምጽ ለልማት እና ሰላም የወገነ፣ የኢትዮጵያን ብሩህ ዘመን ዕውን ለማድረግ ያለመ እንደሆነ አይተናል ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን