
ባሕር ዳር: መስከረም 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ ነው።
ዛሬ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሕዝባዊ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል። ግድቡ የኔ ነው፣ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሠራራት ምልክት ነው፤ ግድባችን የመቻል ማሳያ ነው፤ የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብስራት ነው፤ ሕዳሴ ግድብ፣ በግድቡ የተባበረ ክንድ ለብልጽግናችን ይተጋል የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
ግድባችን የኅብረ ብሔራዊነታችን እና አንድነታችን መገለጫ ነው፤ ሕዳሴ በደም የከበረ በላብ የታሰረ ነው ብለዋል ሰልፈኞቹ።
ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ ዱራሜ ከተማ፣ በቁሊቶ ከተማ፣ በቡታጅራ ከተማ፣ በወልቂጤ ከተማ፣ በወራቤ ከተማ፣ በሳጃ ከተማ ፣ በቆሼ ከተማ፣ በሙዱላ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!