የሕግ ማስከበር ሥራዎች ውጤት እያመጡ ነው።

23

ደብረ ማርቆስ: መስከረም 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን አሥተዳደር በጸጥታ እና የሕግ ማስከበር ተግባራት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው።

ውይይቱ በ2017 በጀት ዓመት የተሠሩ የጸጥታ ተግባራትን በመገምገም የቀጣይ ሥራዎችንም ለማመላከት እንደሚያስችል ተገልጿል።

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ባንተላይ ደምሰው ከዚህ በፊት በነበረው የሕግ ማስከበር ሥራ ላይ የነበሩ ጥንካሬ እና ክፍተቶችን ለመለየት እና ለቀጣይ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫም ለማስቀመጥ አላማ ያደረገ መኾኑን አስረድተዋል።

ኅብረተሰቡ የሰላም ባለቤት እየኾነ ነው ያሉት ምክትል ኀላፊው የጸጥታ መዋቅሩ ከሕዝቡ ጋር ተቀናጅቶ የቀጣይ ክፍተቶችን በመሙላት የሕዝቡን ሰላም መመለስ ይጠበቅበታል ብለዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ ከየወረዳዎች የመጡ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የሕግ ማስከበር ሥራዎች ውጤት እያመጡ መኾናቸውን ጠቅሰዋል። ሕዝቡን ያሳተፈ ሰላምን የማረጋገጥ ተግባራት በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል ይጠበቃልም ብለዋል። ጥምር የጸጥታ ኀይሉም ከሕዝብ ጎን ኾኖ የሕግ ማስከበር ተግባራትን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በውይይት መድረኩ የዞን ከፍተኛ እና መካከለኛ መሪዎችን ጨምሮ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እየተሳተፉ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ያስፈተናቸውን ሁሉንም ተማሪዎች ማሳለፉን አስታወቀ።
Next articleበአማራ ክልል ለበርበሬ ምርት ምን ያህል ትኩረት ተሰጥቷል ?