የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናት ቁጭት ማብቂያ፣ የአብሮነት እና የአንድነት ውጤት ነው፡፡

5
ደብረ ማርቆስ፡ መስከረም 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ቀራንዮ ንዑስ ከተማ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ሕዝቡ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፏል።
‎የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቁ የጠላቶችን አንገት ያስደፋ እና ወዳጆችን ያስደሰተ መኾኑንም ጠቁመዋል።
የግድቡ ግንባታ ተጠናቅቆ ለምረቃ በመብቃቱም መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሁሉም ኢትዮጵያውያን በርብርብ እንዳለቀ ሁሉ ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም በጋራ መቆም ይገባል ነው ያሉት፡፡
‎የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ማማሩ ዐይንአበባ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናት ቁጭት ማብቂያ፣ የአብሮነት እና የአንድነት ውጤት፣ የመቻል ምልክት ዳግም ዓደዋ ነው ብለዋል፡፡
ዋና አሥተዳዳሪው የግድቡ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በቀጣይም ሌሎች መሰል ፕሮጀክቶችን እየሠራች የምታጠናቅቅ እና የምትበለጽግ ሀገር መኾኗን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦
Next articleየትምህርት ዘርፉን መደገፍ የነገ የሀገር ተስፋዎችን ማነጽ ነው።