የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

7
ተፈጥሮን እንደ ዐይኑ ብሌን መንከባከብ እና ማልማት ለሚያውቀው የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ሕዳሴ ልዩ ትርጉም አለው።
ውኃ ለኦሮሞ በሕይዎቱ፣ በባሕሉ፣ በታሪኩ እና በሕዝባዊ እሴቶቹ ሁሉ ትልቅ ቁርኝት ያለው የማንነት ቀለሙ ነው።
በታላቁ ወንዛችን ዓባይ ላይ ለተገነባው የሕዳሴ ግድብ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞቸ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ከደስታ የተሻገረ በመተባበር የመፈጸም አቅምን የሚያሳይ ነው።
በድጋፍ ሰልፎቹ የተስተጋቡት ድምጾችም ልማትን የመናፈቅ ሰላምን አብዝቶ የመፈለግ፣ በመደመር የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመንን በብዙ ድሎች የማጽናት ብርቱ መሻቶች እንደሆኑ አይተናል፡፡
Previous articleተማሪዎችን በትምህርት ቁሳቁስ በመደገፍ ትውልድ የመገንባት ሀገራዊ ኀላፊነታችንን እንወጣ።
Next articleየታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናት ቁጭት ማብቂያ፣ የአብሮነት እና የአንድነት ውጤት ነው፡፡