በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር 16 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል ተሸፍኗል።

4
ደብረ ማርቆስ፡ መስከረም 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በ2017/18 የምርት ዘመን ከ16ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል አይነቶች ተሸፍኗል።
ከዚህም ውስጥ ከ650 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለመሠብሠብ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑንም የከተማ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኀላፊ መለሰ ሙላት ገልጸዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ በዘር ከተሸፈነው ውስጥ ከ9 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በጤፍ እና ስንዴ ክላስተር መሸፈኑን መምሪያ ኀላፊው ጠቁመዋል።
ምርታማነትን ለማሳደግ ከእርሻ ሥራ ጀምሮ የክትትል እና ድጋፍ ሥራዎች ሢሠሩ መቆየታቸውንም ተናግረዋል።
ኀላፊው ተባይን ለመከላከል በተሠራው ሥራ በቆሎ ላይ ተከስቶ የነበረውን የአገዳ ቆርቁር ተባይ በኬሚካል ርጭት መቆጣጠር ተችሏል ነው ያሉት።
የአረም ቁጥጥር እና የተባይ አሰሳ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መኾኑን ያብራሩት ኀላፊው ለኬሚካል እና ፀረ አረም አቅራቢዎች እና ለአርሶ አደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ተሠርተዋል ብለዋል።
የአፈር ለምነትን ለማሻሻል እና አሲዳማነትን ለመቀነስ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑንም አብራርተዋል።
ከ2 ሺህ 200 ሜትር ኪዩብ በላይ ኮምፖስት ለማዘጋጀት እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል። ኀላፊው ከ5 ሺህ ኩንታል በላይ ኖራ በማሰራጨት አሲዳማነትን ማከም ተችሏልም ነው ያሉት ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየሕግ ታራሚዎችን በሥነ ልቦና እና በሥራ ክህሎት ለማብቃት የሚደርገው ጥረት የሚበረታታ ነው።
Next articleሕዳሴ የአንድነት እና የኅብረ ብሔራዊነት ማሕተም ነው።