
ባሕር ዳር: መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መጠናቀቅ ተከትሎ በግሽ ዓባይ ከተማ የደስታ እና የምስጋና ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ “የአይቻልምን ጥቁር መጋረጃ የቀደደ፤ የእንችላለንን መንፈስ ለመላ ኢትዮጵያውያን ያላበሰ ዳግማዊ ዓድዋ” የተገለጠበት ፕሮጀክት እንደኾነ በዕለቱ ተነስቷል።
ግድባችን የአይበገሬነት ተምሳሌት፤ የጋራ ህልማችን የተፈታበት፤ አይችሉም ሲሉን ችለን የተገኘንበት፤ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ዕውን ኾኖ ያየንበት እንደኾነም በሰልፈኞች ተንጸባርቋል።
ቀኑ በፈረስ ጉግስ እና በሌሎች ዝግጅቶች ደምቆ ውሏል።
ሰልፉ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!