“ግድቡ ከደብተር እና ስክብሪቶ መግዣየ ቀንሼ የደገፍኩት ትልቅ ስጦታየ ነው” ተማሪ ፋሲካ

14

ሰቆጣ፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ የድጋፍ ሰልፍ በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል።

ነዋሪዎቹ የተለያዩ መልዕክቶችን በሕዝባዊ ትዕይንቱ ላይ አሰምተዋል። ተማሪዎችም የዚህ ሕዝባዊ ትዕይንት አካል ነበሩ።

ተማሪ ፋሲካ አወጣ የ6ኛ ክፍል ተማሪ ስትኾን የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ለመሳተፍ ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር ወጥታለች።

ተማሪዋ “የሕዳሴ ግድብን ከደብተር እና ከስክብሪቶ መግዣየ ቀንሼ የደገፍኩት ትልቅ ስጦታየ ነው” ብላለች።

ዓባይ ተገድቦ በመጠናቀቁ እንደተደሰተች የገለጸችው ተማሪ ፋሲካ ለታዳጊ ተማሪዎች ስለሀገራቸው ታሪክ እና ጀግንነት ሰምተው ሳይኾን ዐይተው እንዲናገሩ ዕድል የከፈተ ነው ብላለች።

የተማሪ ሰልፈኞችን ስትመራ አሚኮ ያገኛት ተማሪ ኤልዳና ኃይሉ የሕዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ መደሰቷን ገልጻለች።

ታዳጊዋ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክቷንም አስተላልፋለች። በቀጣይም መሰል የልማት ሥራ ለመሥራት የሚያነሳሳ እንደኾነም ነው የተናገረችው።

ተማሪ ዘርፌ ካሳ በበኩሏ የሕዳሴው ግድብ መላው ኢትዮጵያውያን በጋራ የገነቡት የሀገር ጸጋ ነው ብላለች።

ቀደምት አባቶች በዓድዋ ያሳዩትን የአሸናፊነት ታሪክ የዛሬው ትውልድም በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ አሳይቷል ብላለች።

ዘጋቢ ፦ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዳሴ አኩሪ ገድል የሚዘከርበት የአሸናፊነት ብራና ነው።
Next articleሕዳሴ ግድብ የአይቻልምን ጥቁር መጋረጃ የቀደደ ዳግማዊ ዓድዋ ነው።