
ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤልያስ አበበ ሕዳሴ የአሸናፊነት ማሳያ፣ የብልጽግና ጉዞ ማብሰሪያ እና በአንድነት ማሳካት የማንችለው እንደሌለ ያሳየ ዳግማዊ ዓድዋ ነው ብለዋል።
በኅብረት የማንችለውና የማናሳካው አይኖርም ያሉት ኀላፊው በኅብረት ችለናል፤ ዓባይ የብልጽግናችን ጅማሮ ነው፤ በቀጣይም በርካታ ሥራዎችን እንሠራለን ነው ያሉት።
ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የዚህ ዘመን ትውልድ አኩሪ ገድል የሚዘከርበት የአሸናፊነት ብራና ነው ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን