
ወልድያ: መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሠራራት ምልክት ነው” በሚል መሪ መልዕክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ በወልድያ ከተማ የደስታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
የሰሜን ወሎ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የበላይ ጠባቂ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ በዕለቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዓባይ እንዲገደብ አባቶቻችንን ያነሳሳ፤ እኛ ልጆቻቸው እንድንፈጽመው ላበረታን እግዚአብሔር ይመስገን ብለዋል ብጹዕነታቸው።
ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ሲያስቡ ዓባይን መገደብ ወሳኝ መኾኑ ታያቸውና አቀዱ ብለዋል። ከፍጻሜ ሳያደርሱት አለፉ ነው ያሉት። እኛ ልጆቻቸው ዕቅዳቻውን ተረክበን በእኛው ገንዘብ፣ በእኛው ጉልበት፣ በእኛው ዕውቀት ዕቅዳቸውን ለፍጻሜ አበቃን ነው ያሉት።
ሀገራችን ሳንሰጣት አትሰጠንምና፣ ሳናሳድጋትም አታሳድገንምና ቀሪ ሥራዎችን በአንደነት እና በፍቅር ተባብረን ልንሠራ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
“ፈጣሪ ለዚህ ስላበቃን እናመሰግነዋለን” ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!