
ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረማርያም ከሰም ወረዳ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
👉 ግድባችን ተጠናቅቋል፤ የጠላቶቻችን ሴራ በኢትዮጵያዊ አርበኝነት እሳት ተቃጥሎ ከስሟል።
👉 ግድባችን ለተፋሰሱ ሀገራት በረከት እንጂ ጉዳት አያመጣም።
👉የውጭ ተጽዕኖ ያልበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ የቆመ ግድብ።
👉 ግድቡን ማጠናቀቅ የአሸናፊነት ድል አክሊል መድፋት ነው።
👉 ግድባችን የዓባይ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ሰንደቅ።
👉 ግድባችን የይቻላል መንፈስ እርሾ የቁጭት ታሪካችን ማብሰሪያ ታሪክ ነው።
👉 ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን ምሰሶ ነው የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች መተላለፋቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን