
ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁን የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እና መሐል ሜዳ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
👉 ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን የአይቻልም መንፈስን የሰበርንበት ዳግም የዓድዋ ድል ነው።
👉የሕዳሴ ግድባችን እኛ ኢትዮጵያውያን ወደ ዳግም ትንሳኤ የምንሸጋገርበት ልዩ ፀጋችን ነው።
👉 የሕዳሴ ግድብ የብልጽግናችን አሻራ ነው።
👉 በግድቡ የተባበረ ክንድ ለብልጽግናችን ይተጋል።
👉ግድባችን የዓባይ ዘመን ትውልድ ትክክለኛ ሀሳብ፣ በትክክለኛ ጊዜ የገነባው ዘመን ተሸጋሪ ቅርስ ነው
👉 ግድባችን በኢትዮጵያዊነት ኅብር ፀንቶ የመቆም አሸናፊነታችን ኒሻን ነው የሚሉ እና ሌሎች
መልዕክቶች መተላለፋቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
