የሕዳሴ ግድብ በራስ አቅም የተገነባ የአንድነት እና የአብሮነት ውጤት ነው፡፡

14

ደብረ ማርቆስ፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ እና ሞጣ ከተማ አሥተዳደር በጋራ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በድጋፍ ሰልፉ ሕዝቡ የተለያዩ መልዕክቶችን አሰምቷል።

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ላይ ግንባታው ተጠናቅቆ ለምረቃ በመብቃቱ መደሰታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ማማሩ ዓይንአበባ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናት ቁጭት ማብቂያ፣ የአብሮነት እና የአንድነት ውጤት፣ የመቻል ምልክት እንደኾነም ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጣይም ሌሎች መሰል ፕሮጀክቶችን እየሠራች የምታጠናቅቅ እና የምትበለጽግ ሀገር መኾኗን ያሳየ እና ዳግም ዓደዋ የተደገመበት ተግባር ነው ብለዋል፡፡

የሞጣ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ፀሐይ ወንድም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ንቅናቄ ፈጥሮ ጉልበቱን እና ገንዘቡን አፍስሶ ገንብቶ ለምረቃ አብቅቶታል ነው ያሉት፡፡

ግድቡም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን ለጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ኾኖ የሚቆይ ገድል እንደኾነም አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የታየውን አንድነት በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም ሊደግሙት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዳሴ የአንድነታችን እና የአብሮነታችን ምሰሶ ነው።
Next articleግድቡ በኢትዮጵያዊነት ኅብር ፀንቶ የመቆም የአሸናፊነት ኒሻን ነው።