
ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ
በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
👉በኀብረት ችለናል።
👉የሕዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ ማንሠራራት ምልክት።
👉ግድባችን የመቻል ማሳያ የማንሠራራት ጅማሮ ምልክት።
👉ግድባችን በራስ አቅም በአፍሪካዊነት ኩራት የተገነባ እውነት።
👉 ግድባችን የዓባይ ዘመን ትውልድ አኩሪ ገድል የሚዘከርበት የአሸናፊነት ብራና።
👉 ግድባችን የኅብረ ብሔራዊነታችን እና የአንድነታችን መሠረት።
👉 ግድባችን የመነሳት ደወል ብስራት የኢትዮጵያዊነት ድምቀት።
👉በቁርጥ ቀን በጽናት እንድንቆም ያደረገን የአንድነታችን ውል መቀነት።
👉ግድባችን ተጠናቅቋል፣ የጠላቶቻችን ሴራ በኢትዮጵያዊ አርበኝነት እሳት ተቃጥሎ ከስሟል።
👉ግድባችን ለተፋሰሱ ሀገራት በረከት እንጂ ጉዳት አያመጣም።
👉 የውጭ ተጽዕኖ ያልበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ የቆመ ግድብ።
👉 ግድቡን ማጠናቀቅ የአሸናፊነት ድል አክሊል መድፋት ነው።
👉ግድባችን የይቻላል መንፈስ እርሾ የቁጭት ታሪካችን ማብሰሪያ ታሪክ።
👉ግድቡ የኔ፣ ያንቺ፣ የአንተ የኛ ነው። የሀብታችንና የክብራችን ምንጭ ነው የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
ከአማራ ሳይንት ወረዳ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሰልፈኞቹ ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን ምሰሶ ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
