
ደባርቅ፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን ተከትሎ ሕዝባዊ ሰልፍ በዳባት ከተማ እና ወረዳ ተካሂዷል።
በሰልፉ መርሐ ግብር የተገኙት የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እና ለምረቃ መብቃት በቀጣይ ሌሎች ሀገራዊ የታቀዱ የልማት ሥራዎች እንዲከናዎኑ ተነሳሽነትን ይፈጥራል ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ትልቅ አቅም የፈጠረ ታሪካዊ ቅርስ መኾኑንም አብራርተዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ንጋት ሐይቅ ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻ በመኾን ለዘርፉ ማደግ አስተዋጾ እንደሚያደርጉም አብራርተዋል።
የዳባት ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሀብትሸት ሞገስ የሕዳሴ ግድቡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘር እና ቀለም ሳይለያየው በዕኩል የተሳተፈበት የጋራ ሃብት ነው ብለዋል።
የሕዳሴ ግድብ ትውልድ በቅብብሎሽ በብዙ ጫና እና ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፈ የከወነው የዚህ ዘመን ድንቅ ታሪክ ስለመኾኑም አብራርተዋል።
በድጋፍ ሰልፉ የተገኙ ተሳታፊዎችም የሕዳሴ ግድቡ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ደስታን የፈጠረ ብስራት ነው ብለዋል።
በቀጣይ ለሚከናዎኑ ሀገራዊ የልማት ሥራዎችም መነሳሳትን እንደሚፈጥር ነው የተናገሩት።
በቀጣይም ዘላቂ ሰላምን በማጽናት ለሀገራዊ የስኬት ጉዞ ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
