
ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን የስናን ወረዳ ነዋሪዎች የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅ አስመልክቶ የደስታ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል። ነዋሪዎች ደስታቸውን በተለያዩ መልእክቶች ገልጸዋል።
ከስናን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው ነዋሪዎች ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችን እና የአብሮነታችን መሰሶ ነው የሚሉና ሌሎች መልእክቶችን በጋራ አሰምተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ከፍታ ዳግም ያሳየንበት ነው ብለዋል ነዋሪዎች።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
