የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በኢትዮጵያ ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ ከፍቷል።

7

ወልድያ፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ሀራ ከተማ አሥተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

የሀራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ አዲስ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅ በኢትዮጵያ ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ መክፈት መቻሉን ተናግረዋል።

ይህ ታላቅ ሥራ ሕዝብን ከድህነት እና ከግጭት አዙሪት አላቅቆ ወደ ብልጽግና የትብብር ሥራ ለመሸጋገር ወሳኝ መኾኑን ነው የጠቆሙት።

በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀራ ከተማ ነዋሪዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና የሰላም ዘብ የጸጥታ ኀይሎች ተሳትፈዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ ነገ ለምትሠራቸው ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መነሻ ነው” የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች
Next articleታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ከፍታ ዳግም ያሳየንበት ነው።