“የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ ነገ ለምትሠራቸው ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መነሻ ነው” የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች

13

ደብረ ብርሃን: መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዛሬው እለት የግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ በደብረ ብርሃን ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄዷል፡፡

በሰልፉ ላይ የታደሙ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሀገር የምንናፍቀውን የተሟላ እድገት ለማስመዝገብ የሕዳሴው ግድብን የመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ያስፈልጉናል ብለዋል፡፡

ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ የተረባረቡ እጆች በቀጣይም መንግሥት በቅርቡ ይፋ ላደረጋቸው ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ዳግም ታሪክ ለመሥራት መዘርጋት እንዳለባቸው ነዋሪዎቹ ሀሳባቸውን ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡

‎በሕዳሴ ግድቡ ግንባታ ኢትዮጵያውያን አንድነትን አሳይተናል፣ በትብብር የመፈፀም አቅማችንን ለክተንበታል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ነዋሪዎቹ ለወል ችግሮቻችን በጋራ መሥራት፣ የጋራ አቅም ሰብስቦ በኅብረት ታሪካዊ አሻራ በማሳረፍ በኩል የድርሻቸውን አበርክቶ ለማድረግ ዝግጁ መኾናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ዘጋቢ:- በላይ ተስፋዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ሕዳሴ የመቻል እና ሠርቶ የማሳየት ጅምር ነው”
Next articleየሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በኢትዮጵያ ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ ከፍቷል።