ሕዳሴ የአሸናፊነት ምልክት ነው።

3

ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ በምዕራብ ጎጃም ዞን በደምበጫ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

የደምበጫ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሙሉቀን መኮነን
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቅ የሀገራችን የድህነት ኩስመና ማብቂያ፣ የዕድገታችን ማማ፣ የቀጣናችን የጅኦ ፖለቲካ መቀየሪያ እና መዘወሪያ ነው ብለዋል።

ሕዳሴ በራስ አቅም ጀምሮ በራስ አቅም የመፈጸም እና የመልማት ብቃት እና አቅም የታየበት መኾኑን ገልጸዋል።

ከደምበጫ ዙሪያ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሕዳሴ የአሸናፊነት ምልክት መኾኑንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠላቶች ከነተባባሪዎቻቸው የዘመናት ሴራቸው በሕዳሴ ግድብ ጤዛ ኾኖ ረግፏል።
Next article“ሕዳሴ የመቻል እና ሠርቶ የማሳየት ጅምር ነው”