
ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ አካሂደዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች የግድቡ ግንባታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለውን ሳይሰስት ለግሶ እንዲገነባ ያደረገው የልፋት ውጤት መኾኑን ተናግረዋል። በመጠናቀቁም መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ መሳይ ወዳጀ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መላ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን፣ ላባቸውን፣ ደማቸውን ሰጥተው ዕውን ያደረጉት የመቻላችን ማሳያ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ የማይደራደሩ በመኾናቸው የሕዳሴ ግድቡ የአንድነታቸው ማሳያ መኾኑን ገልጸዋል።
ሀገራችን በጋራ፣ በአንድነት፣ ችግሮችን በውይይት እየፈታን ልናለማ ይገባል ነው ያሉት።
የላስታ ወረዳ አሥተዳዳሪ ለዓለም ብርሃኑ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዳግማዊ ዓድዋችን ነው፣ ኢትዮጵያውያን ታሪክ የሠራንበት፣ ለትውልድ ታላቅ ገድል ያቆምንበት ዕለት ነው ብለዋል።
ከላሊበላ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የሕዳሴ ግድቡ የትውልድ ሁሉ ድልና የአፍሪካውያን ተስፋ መኾኑን አንስተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
