
ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አስፋው አዱኛ ለብዙ ዘመናት በዓባይ ላይ ሳንጠቀምበት ቆይተናል ብለዋል። አሁን ደግሞ ከብዙ ውጣ ውረዶች በኋላ ተጠናቅቆ ለመመረቅ በመብቃቱ እንኳን ደስ ያለን ነው ያሉት።
የሕዳሴ ግድብን በራስ አቅም ገንብተን ለምርቃት እንዳበቃነው ሁሉ ከሕዝቡ ጋር ሆነን ታሪክ መሥራታችንን በተግባር እናሳያለን ብለዋል።
ከምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በድጋፍ ሰልፉ የታደሙ ሠልፈኞችም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ በመመረቁ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
