
ደብረ ብርሃን: መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጠናቀቅን አስመልክቶ በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
የሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ የሀገሪቱን የይቻላል መንፈስን ያረጋገጠ እና ለቀጣይ ሀገራዊ መነሳሳትን የሚፈጥር እንደኾነ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ተገልጿል።
የሕዳሴው ግድብ የኢኮኖሚ ምንጭ ብቻ ሳይኾን የኢትዮጵያውያን አንድነት፣ የሉዓላዊነት እና የማንሠራራት ታላቅ ምልክት መኾኑንም ሰልፈኞቹ አንስተዋል።
የግድቡ ግንባታ የውጭ ተጽዕኖዎችን እና የውስጥ ፈተናዎችን በጽናት በመሻገር የተገኘ ድል በመኾኑ ደስታችን ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት ነዋሪዎች፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
