
ወልድያ: መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሠራራት ምልክት ነው” በሚል መሪ መልዕክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መመረቅ አስመልክቶ በወልድያ ከተማ የደስታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዷል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች የታላቁ ሕዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ መደሰታቸውን ተናግረዋል። የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን መተባበር ከቻልን መበልፀግ እንደምንችል ያሳያል ብለዋል። በቀጣይም ልማታችንን ለማጠናከር ሰላም አስፍነን አንድነታችንን ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል።
በቀጣይም የወደብ ጉዳያችን መልስ ለማግኘት ትብብራችን ሊጠናከር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የወደብ ጥያቄያችን በሰላም እና በፍትሐዊ አግባብ የሚገኝበትን መንገድ ለማፅናት በትብብር መሥራት አለብን ነው ያሉት።
በሰልፉ ላይ አባቶች ለታዳጊዎች የሀገር አደራ በሰንደቅ ዓላማ ርክክብ ፈጽመዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
