ግድባችን አንድ ሆነን ብዙ፣ ብዙ ሆነን አንድ የሆንበት የሥብጥራችን ማሕተም ነው።

0

ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መጠናቁቁን ተከትሎ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶችን ተላልፈዋል።

👉በኅብረት ችለናል፣

👉የሕዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ ማንሠራራት ምልክት፣

👉ግድባችን የመቻል ማሳያ የማንሠራራት ጅማሮ ምልክት፣

👉የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብስራት፣ ሕዳሴ ግድብ፣

👉በግድቡ የተባበረ ክንድ ለብልጽግናችን ይተጋል፣

👉ግድባችን በራስ አቅም በአፍሪካዊነት ኩራት የተገነባ እውነት።

👉ግድባችን የዓባይ ዘመን ትውልድ አኩሪ ገድል የሚዘከርበት የአሸናፊነት ብራና።

👉ግድባችን የኅብረ ብሔራዊነታችን እና የአንድነታችን መሠረት።

👉ግድባችን የመነሳት ደወል ብስራት የኢትዮጵያዊነት ድምቀት።

👉በጽናት እንድንቆም ያደረገን የአንድነታችን ውል መቀነት!

👉ግድባችን ተጠናቅቋል፣ የጠላቶቻችን ሴራ በኢትዮጵያዊ አርበኝነት እሳት ተቃጥሎ ከስሟል።

👉ግድባችን ለተፋሰሱ ሀገራት በረከት እንጂ ጉዳት አያመጣም

👉የውጭ ተጽዕኖ ያልበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ የቆመ ግድብ።

👉ግድቡን ማጠናቀቅ የአሸናፊነት ድል አክሊል መድፋት ነው።

👉ግድባችን የዓባይ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ሰንደቅ።

👉ግድባችን የይቻላል መንፈስ እርሾ የቁጭት ታሪካችን ማብሰሪያ ታሪክ።

👉ግድቡ የኔ፣ ያንቺ፣ የአንተ የኛ ነው። የሀብታችንና የክብራችን ምንጭ ነው።

👉ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን ምሰሶ።

👉ግድባችን የዓባይ ዘመን ትውልድ ትክክለኛ ሀሳብ፣ በትክክለኛ ጊዜ የገነባው ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን መተላለፋቸውን ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ግድባችን አንድ ሆነን ብዙ፣ ብዙ ሆነን አንድ የሆንበት የሥብጥራችን ማሕተም፤ ግድባችን በኢትዮጵያዊነት ኅብር ፀንቶ የመቆም አሸናፊነታችን ኒሻን፤ ግድባችን፣ ሀገር ወዳድነታችንን ከቃል በላይ የተግባራችን ልሳን ነው የሚሉ መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት በመርጡለ ማርያም ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleበኃይል አቅርቦት ለምትፈተን ሀገር እና ጨለማን ለሚታገል ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መፍትሔ ነው።