
ባሕር ዳር: መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት በምስራቅ ጎጃም ዞን መርጡለ ማርያም ከተማ እና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
ሰልፈኞቹ ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችን እና የአብሮነታችን ምሰሶ ነው፤ በኅብረት ችለናል፤ የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብሥራት ሕዳሴ ግድብ፤ ግድባችን የዓባይ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ሰንደቅ፤ ግድባችን ለተፋሰሱ ሀገራት በረከት እንጂ ጉዳት አያመጣም፤ ግድባችን ተጠናቅቋል፣ የጠላቶቻችን ሴራ በኢትዮጵያዊ አርበኝነት እሳት ተቃጥሎ ከስሟል እና ሌሎችንም መልዕክቶችን አሰምተዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ በሁለቱም አሥተዳደር የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች እና አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አርሶ አደሮች፣ ተማሪዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የባሕል ኪነት ቡድን አባላት፣ የአባት አርበኞች፣ መምህራን፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የመከላከያ እና የጸጥታ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
መረጃው የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን